የሰቆጣ ወረዳ አለባበስና አጊያጌጥ ለውጥና ቀጣይነት

  • አፀደ ተፈራ
Keywords: ቁሳዊ ባህል፣ አልባሳት፣ አጊያጌጥ፣ ለውጥና ቀጣይነት

Abstract

የዚሀ ጥናት አላማ በቁሳዊ ባህል ስር የሚጠቀሰውን የሰቆጣ ወረዳን አለባበስና አጊያጌጥ ለውጥና
ቀጣይነት መግለጽ ነው፡፡ ጥናቴን በሰቆጣ ወረዳ ላይ እንዳከናወን ያነሳሳኝ ምክንያትም
በወረዳው አለባበስና አጊያጌጥ ላይ የተጠና ጥናት ባለመኖሩና በሉላዊነትና ‹‹በዘመናዊነት››
ምክንያት ሀገረሰባዊ አለባበሱና አጊያጌጡ እየቀነሰና በሌሎች ዘመናዊ አልባሳትና አጊያጌጥ
እየተተካ በመሄዱ፣ የማህበረሰቡ መገለጫነት ሊጠፋ ስለሚችል እንዲሰነድ ለማድረግ ነው፡፡
የጥናቱ ዘዴ ዓይነታዊ ሲሆን በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያነት ያገለግሉትም ቃለ መጠይቅ፣
ምልከታ፣ ቡድን ተኮር ውይይትና ሰነድ ፍተሻ ናቸው፡፡ መረጃው የተሰበሰበው በመስክ ጉዞ ነው፡
፡ የጥናቱ ግኝት እንደሚያመለክተው ባህላዊ አለባበሱና አጊያጌጡ ባሁኑ ጊዜ ከሞላ ጎደል
የሚታየው በገጠር አካባቢ እንደሆነ ነው፤ ወደ ከተማ አካባቢ ግን ለውጡ ጎልቶ ይታያል፡፡
ስለሆነም ባህላዊ አለባበሱና አጊያጌጡ ገጽታውን ሳይለቅ እንዲቀጥል ማህበረሰቡና
የሚመለከታቸውው አካላት ለወጣቶች ማስተማርና ጠቀሜታውን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡

Downloads

Download data is not yet available.

References

ከፍያለው መራሒ (ቀሲስ)። (1992)። የሴቶች መንፈሳዊ ህይወት ።አዲስ አበባ፤አርቲስቲክ ማተሚያ
ቤት።
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣የማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ፡፡ (2003) ፡፡
ዓመታዊ የስታቲስቲክስ መጽሔት ፡፡
ጉለሹ በንኑ፣ነሐሴ (1987)‹‹በትንንሽ ኮረት ትልቅ ህድሞ››፣ማህቶት፣8፡፡
ፈቃደ አዘዘ። (1991)። የሥነ ቃል መምሪያ ፤አዲስ አበባ፤ቦሌ ማተሚያ ቤት።
Barre Toelken. (1979 ) The Dynamics of Folklore. Boston: Houghton Mifflin,
Dorson, Richard.M. (1972) ’’ Introduction: Concepts of Folklore and Folk life
studies’’ in Richard. M.Dorson, (ed.).Folklore and Folk life: An
Introduction. Chicago and
London: the University of Chicago Press.1-50. Retrieved from:
eprints.hud.ac.uk
"Folk Arts." 1993. The New Encyclopedia Britannica Macropedia. Chicago:
Encyclopedia Britannica Inc. Vol. 19, PP. 306-338.
Leach, Maria (ed.) (1950).Standard Dictionary of Folklore Mythology, and Legend
Vol.II. NewYork: New York Publisher
Pankhurst, Richard. ( 1982.) History of Ethiopian Towns from the Middle Ages to
the Early Nineteenth Century. Wiesbaden: Franz Steiner Verlag Gmbh.
Sims ,Martha C. & Martine Stephens. (2005).Living Folklore: An introduction to
the Study of people and their traditions. Logan, Utah: Utah University
Press.
Viduka J.Andrew (2012). Material Culture. Thailand: Published by UNESCO
Bangkok.
Wilson, Wiliam, A. (1989).’’ Documenting Folklore”, in Elliott Oring, (ed.) Folk
Groups and Folklore Genres: An Introduction. Logan, Utah: Utah State
University Press. 225-254.
Published
2018-06-25