ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
http://ejol.ethernet.edu.et/index.php/AELC

“ZENA LISSAN” is a bilingual, biannual and peer-reviewed journal which publishes original empirical studies, literature reviews, theoretical articles, methodological articles, book reviews, dissertation and thesis abstracts, synopsis of major research, short communications, commentaries, and other relevant issues in the area of languages and cultures.

en-US
ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
2222-6028

የቦረና ኦሮሞ የበኩር ልጅ ስም ስያሜ በዓል ክዋኔ አውድ
http://ejol.ethernet.edu.et/index.php/AELC/article/view/1207

ፎክሎር ህዝቦች በመኖሪያ አካባቢያቸውና በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ሁሉ ሲገናኙ የሚከውኑዋቸው ወጎች፣ እምነቶች፣ ህዝባዊ ጥበቦችንና ሌሎችንም ያካትታል። ከነዚህ አንዱ
የሆነው የስም ስያሜ አንድ ህፃን ከነበረበት ደረጃ ወደ ተከታዩ ወይም ወደ ሌላ ደረጃ መሻገሩንና ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀሉን ያመለክታል። ይህን መሰሉን የደረጃ ሽግግር
የሚያመለክተው ይህ ጥናት በኦሮሚያ ክልል፣ በቦረና ዞን በሚገኘው ቦረና ኦሮሞ የበኩር ልጅ ስም ስያሜ በዓል (ጉቢሳ) ላይ ያተኩራል። ቦረናን ጨምሮ የኦሮሞ ባህልና ወግ በአብዛኛው
ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየው በቃል ነው፡፡ እነዚህ በቃል ያሉ አብዘኛዎቹ ባህልና ወጎች ወይም የፎክሎር ዘርፎች አልተጠኑም። በባህሪ ተለዋዋጭ በመሆናቸው በቃል
ሲያስተላልፉ የነበሩት የህዝቡ ባህላዊ፣ ማህበራዊና መንፈሳዊ እውቀቶችና እሴቶች፣ ይለወጣሉ፣ ይረሳሉ፣ ይጠፋሉ። ስለዚህ አነዚህ አሁን በመከወን ያሉና የመለወጥ እድላቸው ሰፍቶ የሚታዩ
ባህላዊ ክዋኔዎች ተጠንተው በጽሑፍ ቢቀመጡ ነባሩን እውቀት ለትውልድ ማስተላለፍ ይቻላል። በመሆኑም ይህ ሀሳብ ለጥናቱ አነሳሽ ምክንያት ሆኗል። በጥናቱ የቦረና አሮሞዎች የበኩር ልጅ
ስም ስያሜ በዓል ሲያከብሩ ምንምን ክዋኔዎች ይከውናሉ? በየክዋኔዎቹ ምንምን የፎክሎር ዓይነቶች ይቀርባሉ ወይም ይካተታሉ? በየክዋኔዎቹ ውስጥ የህዝቡ ተሳትፎ ምን ይመስላል?
የሚሉት ጥያቄዎች ተመልሰዋል። የጥናቱ ዋና ዓላማ የቦረና ኦሮሞ ማንነትና አተያይ ማሳያ ከሆኑት የባህል ዘርፎች ውስጥ የበኩር ልጅ ስም ስያሜ በዓል ክዋኔዎች በውስጣቸው ከያዙት
የፎክሎር ዓይነቶች፣ ከሚኖራቸው ተምሳሌታዊ ፍችና ከሚያስተላልፉት መልዕክት አንፃር በመግለፅና በመተንተን መዝግቦ ማቆየት ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት በባህል እውቀታቸው
የላቁ ናቸው ተብለው ከሚታወቁት አባቶች ቁልፍ መረጃ አቀባዮች በታላሚ ናሙና ከተመረጡ በኋላ፣ (1)በቃለመጠይቅ (2) በምልከታ እና (3) ተሳትፎ ምልከታ ዘዴዎች መረጃዎቹ
ተሰብስበዋል። ፎክሎር በባህሪው ዘርፈ ብዙ የጥናት ክፍል በመሆኑ የተለያዩ የትንተና አንፃሮች በጥምር መጠቀም ይጠይቃል። ስለሆነም ለዚህ ጥናት መረጃዎች መተንተኛ በዋንኛነት
የተመረጡት የአውድና የክዋኔ የትንተና አንፃሮች ናቸው፡፡ በነዚህ የትንተና አንፃሮች በክዋኔዎች ሂደታዊ አፈፃፀም ባለጉዳዩ የመለየት፣ የሽግግር እና የመቀላቀል ደረጃዎችን ሲሻገር እንዲታይ፣
ክዋኔዎቹና በየክዋኔዎቹ የሚቀርቡት የፎክሎር ዓይነቶች ምንነትና ፍካሬያዊ ትርጓሜያቸውም እንዲሁ ጎልተው እንዲወጡ ተደርገዋል። ባጠቃላይ የበኩር ልጅ ስም ስያሜ በዓል ጉቢሣ
የተለያዩ የፎክሎር ዓይነቶች ማለትም ሥነቃል፣ ቁሳዊ ባህል፣ ሀገረሰባዊ ልማድና ትውን ጥበባትን አካቶ በመያዝ የቦረናን ኦሮሞ እምነት፣ አተያይ፣ ጠንካራ የርስ በርስ ግንኙነት፣ የምጣኔ
ሐብት አገነባብ ዘዴዎችና የባህል ህግጋት ጥበቃ ዘዴዎቹ ጎልተው እንዲታዩ ያደረገ በዓል ነው፡፡

ደስታ አማረ
Copyright (c) 2019 ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
2018-06-20
2018-06-20
27 1
1
30

በኢትዮጵያ የአራት ብሔራውያን ክልላውያን መንግሥታት የሕዝብ መዝሙሮች ይዘት ትንተና
http://ejol.ethernet.edu.et/index.php/AELC/article/view/1208

“የኢትዮጵያን ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመሠረቱት” ብሔራውያን ክልላውያን መንግሥታት
በየሕገ መንግሥታቸው የየራሳቸው የሕዝብ መዝሙር እንደሚኖራቸውና በሕዝብ መዝሙሮቻቸው
ሊንፀባረቁ የሚገባቸውን ይዘቶች ደንግገዋል፡፡ ድንጋጌያቸውን ተግባራዊ በማድረግ የራሳቸው ክልል
ሕዝብ መዝሙር ያላቸው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ የዐማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ብቻ ናቸው፡፡ የዚኽ ጥናት
ትኩረትም በተጠቀሱት ብሔራውያን ክልላውያን መንግሥታት የሕዝብ መዝሙሮች ላይ ነው፡፡ ይኽን
ጥናት ማካኼድ ያስፈለገበት ምክንያት፣ በብሔራውያን ክልላውያን መንግሥታት የሕዝብ መዝሙሮች ላይ
የተደረገ ጥናት አለመኖርና ክፍተቱን ለመሙላት ምርምር ማድረግ አስፈላጊ በመኾኑ ነው፡፡ የጥናቱ ዐቢይ
ዓላማ የአራት ብሔራውያን ክልላውያን መንግሥታት የሕዝብ መዝሙሮች የሀገራችንን ታሪካዊ፣
ፖለቲካዊና ባህላዊ ኹኔታዎች ምን ያኽል እንዳንጸባረቁና በኅብረተ ሰቡ ውስጥ ለማስረጽ የተደረገውን
ጥረት መመርመርና ይዘቶቹን መተንተን ነው፡፡ ከዚኽ ዐቢይ ዓላማ የሚመነጩ ዝርዝር ዓላማዎችም፣
ብሔራውያን ክልላውያን መዝሙራቱን ለመድረስ ያነሣሡ ታሪካዊና ፖለቲካዊ ምክንያቶችን መመርመር፣
ብሔራውያን ክልላውያን መንግሥታት በየሕገ መንግሥታቸው ስለብሔራዊ ክልላቸው የሕዝብ መዝሙር
የደነገጓቸው ይዘቶች ምን ያኽል በየመዝሙሮቹ እንደተንጸባረቁ መመርመር፣ መተንተን፣ የሕዝብ
መዝሙሮቹ ብሔራዊ ማንነትን ለመገንባት (ለማጠናከር) (national identity building and
strengthening) እንዲሁም ሀገራዊ አንድነትን ለማጎልበልበት ያላቸውን ጠቀሜታ፣ ብሔራውያን
ክልላውያን የሕዝብ መዝሙራቱ ከፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ጋር
እንዴት ተጣጥመው አገልግሎት እንደሚሰጡ መፈተሽና የሕዝብ መዝሙሮቹ የሚገልጹዋቸውን ርዕዮተ
ዓለሞች መመርመር የሚሉት ናቸው፡፡ እነዚኽን ዓላማዎች ለማሳካት ጥናቱ የሚመልሳቸው ጥያቄዎች፡-
ብሔራውያን ክልላውያን መዝሙሮቹን ለመድረስ ያነሣሡ ምክንያቶች ምን ምን ናቸው? ብሔራዊ ክልላዊ
መዝሙሮቹ የተደረሱበትን ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊና ማኅበራዊ እውነታ ምን ያኽል አንጸባርቀዋል?
በብሔራውያን ክልላውያን ሕገ መንግሥታት ስለሕዝብ መዝሙሮች የተደነገጉት ይዘቶች በሕዝብ
መዝሙሮቻቸው እንዴት ተንጸባረቁ? በብሔራውያን ክልላውያን የሕዝብ መዝሙሮች አማካይነት
በወጣቶች አዕምሮ እንዲሰርፁ የተደረጉትን ርዕዮተ ዓለሞች ብሔራዊና ሀገራዊ ጠቀሜታ ምን ያኽል ነው?
የሚሉት ናቸው፡፡ ጥናቱ፣ በተጠቀሱት ብሔራውያን ክልላውያን የሕዝብ መዝሙሮች ላይ ማተኰሩ
የተለያዩ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ የብሔራውያን ክልላውያን መዝሙራቱ ታሪክ ምን እንደሚመስል
ለመገንዘብ፣ የብሔራውያን ክልላውያን መዝሙራቱን ተግባርና አገልግሎት ለመረዳት በተለይም የብሔራዊ
ማንነትን ለመገንባት (national identity building and strengthening) ያላቸውን ሚና፣
(በብሔራውያን ክልላውያን የሕዝብ መዝሙሮች አማካይነት በወጣቶች አዕምሮ እንዲሰርፁ የተደረጉትን
ርዕዮተ ዓለሞች ለመረዳት ያስችላል፡፡) ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከርና ለማጎልበት ያላቸውን ጠቀሜታ፣
እንዲሁም ብሔራዊ ክልላዊ መዝሙራቱ ከፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ ብሔራዊ
መዝሙር ጋር እንዴት ተጣጥመው አገልግሎት እንደሚሰጡና በየሕገ መንግሥታቸው የሕዝብ
መዝሙሮቻቸው እንዲንጸባረቁ የተደነገጉት ይዘቶች እንዴት እንደተንጸባረቁ ለመረዳት ያስችላል፡፡
እንዲሁም፣ ወደ ፊት ለሚደረጉ ተመሳሳይ ጥናቶች መነሻነት ያገለግል፡፡ የዚኽ ጥናት የመረጃ ምንጮች
ጥናቱ ትኩረት ያደረገባቸው ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት ሕገ መንንግሥቶች፣ የብሔራዊ ክልላዊ
መንግሥታት የሕዝብ መዝሙሮች፣ ዐዋጆች፣ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥቱን የሚመሩት

መስፍን መሰለ
Copyright (c) 2019 ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
2018-06-25
2018-06-25
27 1
31
74

የሃይማኖት መቻቻልን ማስተዋወቅ ለሰላማዊ አብሮነት በአርሲ ዞን ማሳያነት
http://ejol.ethernet.edu.et/index.php/AELC/article/view/1209

የጥናቱ ዋና አላማ፣ በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት መካከል በሰላማዊ አብሮነት ለመኖር
ያስቻሏቸው የመቻቻል መገለጫ ፎክሎሮችን ማስተዋወቅ ይሆናል። ኢትዮጵያ በብሔረሰቦቹዋ
ውስጥና መካከል በታሪክ የተገነባው የብዝኀ-ባህል የግንኙነት መስተጋብር ባሕርያት ምን
እንደሚመስሉ ተጠንተው አልተገለፁም፡፡ አይታወቁም፡፡ የዚህ ጥናት ዋና ትኩረት በሆነው
በአርሲ ዞን፣ በሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ውስጥ የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ
ማህበረሰቦች መካከል ባለው የመቻቻል እሴት ከፎክሎር አንፃር ማሳየት ነው። በክርስትና እና
በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል በሰላም ተከባብሮ ለመኖር ያስቻሏቸው የመቻቻል
ፎክሎር ምንድን ናቸው? በአርሲ ዞን በሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ለሰላማዊ አብሮነት
አስተዋጽዎ ያላቸው የመቻቻል ባህላዊ እሴቶች በተለይ እድር፣ ጡት መጣባትና ባህላዊ
እምነት ጥናቱ ያተኮረባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው። በማህበረሰቦች መካከል ያሉትን
የሃይማኖት ልዩነቶች በመቻቻል የሚመሩ፣ በባህል የተደነገጉና የተቁዋቁዋሙ ለዘላቂ ሰላም
መሠረትና ዋስትና ተግባራዊ ሕጎች ሆነው ይሠራሉ፡፡ ባህላዊ እሴቶቹ በተለይም በእስልምናና
በትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ‘መቻቻል’ የሚለውን ፅንሰ-ሀሳብ፣
መርህና ተግብራዊ ድርጊቶች ማለትም፡- አንዱ የሌላውን ኅልውና ተቀብሎ እውቅና መስጠትን፣
መከባባርን፣ መተሳሰብን፣ መረዳዳትን፣ መተባበርን፣ አብሮነትን፣ አንድነትንና ሰላምን፣ ወዘተ፣
የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡

ፍሬህይወት ባዩ
Copyright (c) 2019 ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
2018-06-25
2018-06-25
27 1
75
90

Demonstratives in Silt’e
http://ejol.ethernet.edu.et/index.php/AELC/article/view/1215

This article intended to describe the system of demonstratives in Silt’e.
According to their distribution, forms and functions, demonstratives in
Silt’e categorize in to pronominal, adverbial and manner. Pronominal
demonstratives have two forms: free and complex. The free and complex
forms have two distinctions: proximal and distal. The free demonstrative
pronouns have neutral and focused form. The complex demonstrative
pronouns occur with preposition lə-, tə-and bə-, which indicate a dative,
ablative or comitative and instrumental or locative case of demonstrative
pronouns respectively. Adverbial demonstratives are formed by affixing
morphemes to basic demonstratives. Manner demonstratives are discourse
deictic, they formed by a combination of basic demonstrative pronoun and
simulative morpheme –ku, ‘like.’

Rawda Siraj
Copyright (c) 2019 ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
2018-06-25
2018-06-25
27 1
91
110

የደቂቀ እስጢፋኖስ ዐውደ ንባባዊ ትንታኔ
http://ejol.ethernet.edu.et/index.php/AELC/article/view/1213

የዚህ ጥናት ትኩረት ደቂቀ እስጢፋኖስ(“በህግ አምላክ”) በሚል ርዕስ በጌታቸው ሀይሌ ከግዕዝ
ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ የታተመ መጽሀፍ ነው።
የአባ እስጢፋኖስና የተከታዮቻቸው ገድል በጥቅሉ ደቂቀ እስጢፋኖስ ተብሎ አራት ገድሎችን
በአንድ ጥራዝ አካቶ ለህትመት በቅቷል። የጽሁፉ ዋና አላማ ደቂቀ እስጢፋኖስን በዐውደ ንባባዊ
ስልት መተንተን ይሆናል። በደቂቀ እስጢፋኖስ ገድል ውስጥ የተካተቱት ገድሎች የ15መ/ክ/ዘ
ኢትዮጵያዊያን በተለይም የሃይማኖት መጻህፍትን በማንበብ በመጻፍ እና በመመራመር የላቀ
አስተሳሰብ እንደነበራቸው የሚጠቁሙ ናቸው። አባ እስጢፋኖስ እና ተከታዮቻቸው ከአጼ
ይስሀቅ ጀምሮ እስከ አጼ ናኦድ ድረስ በነበረው ንትርክ ከደረሰባቸው መከራ ተነስተው
ገድላቸውን የጻፉት ተከታዮቻቸው ናቸው። በገድላቸው ውስጥ የምናየው በዘመኑ የነበረውን
የማሰብ ነጻነት ጠቋሚ አሻራዎች ነው። ይህም ጥናት በአውደ ንባባዊ ስልት ገድሉ ውስጥ የተነሱ
ኮዶችን በማፍታታት “ሀሳብን በሀሳብ እና ሀሳብን በስልጣን መርታት” የሚል አብይ ጭብጥ
ተለይቶ ወጥቶለታል። የአባ እስጢፋኖስና የተከታዮቻቸው ገድሎች እንደ ሌሎች ገድሎች ዐውደ
ንባቦቹ የሃይማኖት ናቸው። በአውደ ንባቦች ውስጥ ያሉት ድርጊቶች ሁነቶች እና ሁኔታዎች
ሃይማኖታዊ ናቸው። ሆኖም በእምነት አይን አይተን በእምነት ጆሮ ሰምተን በእምነት ልቡና
አምነን ይሁን ብለን የምናስተናግደው ብቻ አይደሉም። ስለዚህ ደቂቀ እስጢፋኖስ ከገድልነቱ እና
ከስነጽሁፍ ቅርስነቱ ባሻገር በተለያየ የሙያ መስክ ቢጠና፣ ማስረጃዎችን ለይቶ በማውጣት
ለሌሎች የጥናት መስኮች ግብአት በመሆን ያገለግላል።

ፍሬህይወት ባዩ
Copyright (c) 2019 ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
2018-06-25
2018-06-25
27 1
111
125

የሰቆጣ ወረዳ አለባበስና አጊያጌጥ ለውጥና ቀጣይነት
http://ejol.ethernet.edu.et/index.php/AELC/article/view/1214

የዚሀ ጥናት አላማ በቁሳዊ ባህል ስር የሚጠቀሰውን የሰቆጣ ወረዳን አለባበስና አጊያጌጥ ለውጥና
ቀጣይነት መግለጽ ነው፡፡ ጥናቴን በሰቆጣ ወረዳ ላይ እንዳከናወን ያነሳሳኝ ምክንያትም
በወረዳው አለባበስና አጊያጌጥ ላይ የተጠና ጥናት ባለመኖሩና በሉላዊነትና ‹‹በዘመናዊነት››
ምክንያት ሀገረሰባዊ አለባበሱና አጊያጌጡ እየቀነሰና በሌሎች ዘመናዊ አልባሳትና አጊያጌጥ
እየተተካ በመሄዱ፣ የማህበረሰቡ መገለጫነት ሊጠፋ ስለሚችል እንዲሰነድ ለማድረግ ነው፡፡
የጥናቱ ዘዴ ዓይነታዊ ሲሆን በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያነት ያገለግሉትም ቃለ መጠይቅ፣
ምልከታ፣ ቡድን ተኮር ውይይትና ሰነድ ፍተሻ ናቸው፡፡ መረጃው የተሰበሰበው በመስክ ጉዞ ነው፡
፡ የጥናቱ ግኝት እንደሚያመለክተው ባህላዊ አለባበሱና አጊያጌጡ ባሁኑ ጊዜ ከሞላ ጎደል
የሚታየው በገጠር አካባቢ እንደሆነ ነው፤ ወደ ከተማ አካባቢ ግን ለውጡ ጎልቶ ይታያል፡፡
ስለሆነም ባህላዊ አለባበሱና አጊያጌጡ ገጽታውን ሳይለቅ እንዲቀጥል ማህበረሰቡና
የሚመለከታቸውው አካላት ለወጣቶች ማስተማርና ጠቀሜታውን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡

አፀደ ተፈራ
Copyright (c) 2019 ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
2018-06-25
2018-06-25
27 1
126
140