የአመክሮ ሕጎችና አተገባበራቸው በባሕር ዳር ማረሚያ ቤት

  • በላይነህ አድማሱ እጅጉ ረዳት ፕሮፌሰር፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት
  • ዓለሙ ዳኛው ፈለቀ ሌክቸረር፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት
Keywords: አመክሮ፣ ማረሚያ ቤት፣ የእስራት ቅጣት፣ ታራሚ፣ መልካም ጸባይ

Abstract

በኢትዮጵያ አመክሮ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም የሚባል የባሕርይ መሻሻል በማሳየታቸው 2/3ኛውን የእሥራት ጊዜ ካጠናቀቁ በኋላ ቀሪውን የፍርዱን 1/3ኛ ወይም በፍርድ ቤት የሚወሰነውን የሙከራ ጊዜ በአመክሮ ከእስር ተለቅቀው በሙከራ እንዲያሳልፉ የሚደረግበት አሰራር ነው፡፡1 ጥናቱ በተደረገበት በአማራ ብሄራዊ ክልል አንዱ በሆነው የባሕር ዳር ማረሚያ ቤትም ይኸው ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ይሁን እንጂ በአመክሮ አተገባበርና ሕጉ ላይ ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ የዚህ ጥናት ዋና ዓላማም በክልሉ አመክሮ አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ የሕግ ክፍተቶችንና በማረሚያ ቤቱ አሉ የሚባሉ የአፈጻጸም ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ ሐሳቦችን ለመጠቆም ነው፡፡ በማረሚያ ቤቱ የአመክሮ ሕጎችና አፈጻጸማቸው ምን እንደሚመስል በአይነታዊ የጥናት ዘዴ ለመመርምር ተሞክሯል፡፡ የጥናቱ መረጃዎችም በሳይንሳዊ መንገድ ተተንትነዋል፡፡ በዚህም መሰረት በወንጀል ሕጉና በአብክመ አመክሮ አሰጣጥ መመሪያ መካከል አለመጣጣምና የሕግና የአፈጻጸም ክፍተቶች መኖራቸውን የጥናቱ ግኝት አሳይቷል፡፡

Downloads

Download data is not yet available.
Published
2016-12-01