የተከፋፈሉ ማሕበረሰቦች (Divided Society) እና የሕገ-መንግስት ንድፍ፤ ኢትዮጵያ በተከተለችው አማራጭ ላይ ምልከታ

  • ጎሳዬ አየለ በሃዋሳ የኒቨርሲት ፣ ሕግ ትምህርት ቤት የሕግ መምህር
Keywords: የተከፋፈለ ማህበረሰብ ፣የስምምነት/ሥልጣን ማጋራት/ ዴሞክራሲ ፣የማሳሳብ ዴሞክራሲ

Abstract

የተከፋፈሉ ማህበረሰቦች የሚያጋጥማቸው አብይ ችግር በማንነት ላይ የተመሰረተ አለመግባባት ወይም ግጭት ነው፡፡ ይህ በቋንቋ ፣ብሄር፣ ኃይማኖት ወዘተ ልዩነት ላይ ተመስርቶ የሚነሳ አለመግባባት ወይም ግጭት ያለባቸው ማህበረሰቦች የተከፋፈሉ ማህበረሰቦች ይባላሉ፡፡ ለነዚህ ማህበረሰቦች በማንነት ላይ ተመስርቶ ለሚነሳው ግጭት ማረቂያ /management/ እንዲሆኑ ከቀረቡት መፍትሄዎች ወስጥ የሕገ-መንግስት ንድፉ ይህን ችግር እንዲቀርፍ አድርጎ መቅረፅ አንደኛው ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በጣም የሚታወቁትና ተወዳዳሪ ንድፍ ያቀረቡት አረንድ ላይፓርትና ሮናልድ ሆሮዊትዝ ናቸው፡፡ ላይፓርት የስምምነት ወይም የአስፈፃሚውን ስልጣን ማጋራት ሕገመንግስታዊ ንድፍ /Consociationalism/ ሲያቀነቅን ሆሮዊትዝ በበኩሉ የማሳሳብ ንድፍን /Centripetalism/ ይደግፋል፡፡ ሁለቱም ፀሀፊዎች የብዙሃን ዴሞክራሲ ንድፍ /Westminster majoritarian democracy/ ለተከፋፈሉ ማህበረሰቦች የማይሰራና እንዳይተገብሩት ቢመክሩም አማራጭ ብለው ያቀረቧቸው ንድፎች ደግሞ በጣም የተለያዩ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሕገ-መንግስት በማንነት ላይ ተመርኩዞ ሊሚነሳ አለመግባበት ወይም ግጭት መፍትሄ አንዲሆን ተብሎ የተቀረፀ ቢሆንም አነዚህ ለተከፋፈሉ ማህበረሰቦች መፍትሄ ይሆናሉ ተብለው ከቀረቡት አማራጭ ንድፎች አንፃር ሲታይ አነዚህ ንድፎችን በተገቢው መጠንና ዓይነት በአጥጋቢ ሁኔታ አላካተተም፡፡ ሕገመንግስቱን የቀረፁት ሰዎች የማሳሳብ ንድፍ ከናካቴው ከግምት ውስጥ አላስገቡም፡፡ የተወሰኑ የስምምነት ወይም የአስፈፃሚውን ስልጣን ማጋራት የሚጠይቀውን ንድፍ አንዳንድ ጉዳዮችን ያካተተ ቢሆንም ዋና ዋና የንድፉ መገለጫዎች የሆኑትን አንደ አስፈፃሚውን ሥልጣን ማጋራት እና ተመጣጣኝ ውክልና የምርጫ ሥርዓት የሚመለከቱትን አላካተተም፡፡ በተከፋፈሉ ማህበረሰቦች ውስጥ ሰላም ማምጣት የሚቻለው ወይም በማንነት ልዩነት ላይ ተመርኩዞ ሊሚነሳ ግጭት ማረቅ የሚቻለው ሁለቱ ፀሃፊዎች እንዳቀረቡት አማራጭ ንድፎች ከሆነ የኢትዮጵያ ሕገመንግሰት ይህን ችግር የሚያስታምም ወይም የሚቀርፍ ንድፍ የለውም፡፡

Downloads

Download data is not yet available.
Published
2016-12-01