በኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ ለአካለ መጠን የደረሰ ሰው ጉዲፈቻ (Adult Adoption) የመፍቀድ አስፈላጊነት፡- አንዳንድ ነጥቦች ከሌሎች አገራት ሕግጋት ተሞክሮ

  • ነጋ እውነቴ መኮንን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት የሕግ ረዳት ፕሮፌሰር
Keywords: ለአካለ መጠን የደረሰ ሰው ጉዲፈቻ፣ የእድሜ ልዩነት፣ ቀደምት ግንኙነት፣ ባህላዊ፣ ትውፊታዊና ታሪካዊ መሠረት፣ ቤተሰባዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ-ልቦዊ ምክንያቶች፣ የቤተሰብ ሕይወት የመከበር መብት

Abstract

ለአካለ መጠን የደረሰ ሰው ጉዲፈቻ የሮማዊያንን ሕግ ጨምሮ በጥንታዊ ሕግጋት ውስጥ ቦታ የነበረው ሲሆን ለአህጉረ አውሮፓና ለኢትዮጵያ የፍትሐ ብሔር ሕግ መሠረት በሆነው እ.አ.አ. በ1804 ዓ.ም በወጣው የፈረንሳዩ የናፖልዮን ሕግ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ እንዲሁም በሂደት በናፖልዮን ሕግ አማካይነት በዘመናዊው የፈረንሳይ፣ የእስፔን፣ የጣልያን፣ የጀርመንና በሌሎች የአውሮፓ አገራት ሕግጋት ውስጥ ለአካለ መጠን የደረሰ ሰው ጉዲፈቻ የተፈቀደ ሲሆን፣ ከዚያም አልፎ በአሜሪካ ግዛቶችና በሌሎች የኮመን ሎው የሕግ ሥርዓት በሚከተሉ አገራት የቤተሰብ ሕግጋት ውስጥ በስፋት እየተሠራበት ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ለአካለ መጠን የደረሰ ሰው ጉዲፈቻ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ትውፊታዊና ማኅበራዊ መሠረት የነበረው ሲሆን፣ ምንጩን በዋናነት ከፈረንሳይ የፍትሐ ብሔር ሕግ ያደረገውና በ1952 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ የፍትሐ ብሔር ሕግ ለጉዳዩ እውቅና ከመንፈግ ባሻገር በወቅቱ ሥራ ላይ ከነበሩ ሌሎች ነባር የአገሪቱ የልማድ ሕግጋት ጋር አብሮ ሽሮታል፤ መሠረታቸውን የ1952 ዓ.ም የኢትዮጵያ የፍትሐ ብሔር ሕግ ያደረጉትና በቀጣይ ተሻሽለው የወጡት የፌዴራልም ሆነ የክልል የቤተሰብ ሕግጋት ተመሳሳይ መንገድ ተከትለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ለአካለ መጠን የደረሰ ሰው ጉዲፈቻን ለመፍቀድ የሚያስችሉ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ትውፊታዊ፣ ማኅበራዊና ሕጋዊ ምክንያቶች አሉ፤ በማለት ይህ አጥኝ ይከራከራል፤ እንዲሁም እነዚህን ምክንያቶች መሠረት በማድረግ አሁን በሥራ ላይ ያለው የቤተሰብ ሕግ እንዲሻሻል አጥኝው ይመክራል፡

Downloads

Download data is not yet available.
Published
2019-06-01