Articles

የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ የተፈፃሚነት ወሰን ከጊዜ አንፃር᎓- በፍርዶች ላይ የቀረበ ትችት

Abstract

ከፍትሐ ብሔር ሕጉ ድንጋጌዎች ጀምሮ በተለያዩ ጊዚያት በሀገራችን በርካታ የገጠር መሬት ሕጎች ታውጀዋል።1 እነዚህ ሕጎች በየዘመናቸው ለመሬት ባለቤቶች በኋላም ባለይዞታዎች የሚሰጡት መብት ወጥነት አልነበረውም፤ አሁንም የለውም፡፡2 ለምሳሌ በአዋጅ ቁጥር 89/1989 መሰረት የመሬት ባለይዞታው መሬቱን ለቤተሰብ አባሉ ብቻ ማውረስ እንደሚችል ተደንግጎ ነበር።3 በአማራ ክልል ከአዋጅ ቁጥር 46/1992 አንፃር ባለይዞታው መሬቱን በኑዛዜ የሚያስተላልፈው ለቤተሰብ አባሉ ወይም ለሚጦረው ሰው ብቻ ነበር፡፡4 በዚህ አዋጅ መሰረት መሬትን ያለ ኑዛዜ በውርስ ማስተላለፍ የሚቻለው ለባለይዞታው የቤተሰብ አባል ብቻ ነበር፡፡

Downloads

Download data is not yet available.

Related articles