Articles

የሁለት ደብዳቤዎች ንፅፅር

Abstract

ይህ ጽሑፍ ዐፄ ቲዎድሮስና አባ እምነቱ የሚባሉ መነኩሴ የጻፏቸውን ደብዳቤዎች ያነጻጽራል፡፡ ንጽጽሩ የይዘትና የቅርጽ ነው፡፡ ቅርጹ ሥነ ልሳናዊ ሲሆን ይዘቱ ማኅበረ - ፖለቲካዊ፣ ባህላዊና ሥነ ልቦናዊ ነው፡፡ ጸሐፊዎቹ ሰበ-ሥልጣን ናቸው፡፡ አንዱ ዓለማዊ ንጉሠ ነገሥትና ኦርቶዶክሳዊ አማኝ፣ ሁለተኛው መንፈሳዊ መነኩሴና ከቶሊካዊ አማኝ፡፡ መነኩሴው የካቶሊክን እምነት ማስፋፋት፣ ዐፄው የኦርቶዶክስን እምነት መጠበቅ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ በሁለቱ መካከል የሥልጣን ቅራኔ ይፈጥራል፡፡ ድብደቤዎቹ የተጻፉት በሁለቱ ጸሐፊዎች ጀርባ ለሚገኙ ሌሎች ሰበ- ሥልጣናት ነው፡፡ መነኩሴው ለፈረንሳይ፣ ዐፄው ለእንግሊዝ ወኪል የጻፏቸው የእርዳታ ጥሪ ናቸው፡፡ ጥሪው መልስ ያጣል፤ ስለዚህም ጭንቀት ይፈጠራል፡፡ ከዚህ የተነሣ ዐፄው በመነኩሴውና በደጋፊዎቻቸው ላይ እርምጃ የውስዳሉ፡፡ መነኩሴውን ያባርራሉ፤ ደጋፊያቸውን ይገድላሉ፡፡ ቅራኔው በግጭት ይቋጫል፤ ግን አይፈታም፣ እስከ ዐፄው ፍጻሜ ድረስ ይቀጥላል፡፡ የደብዳቤዎቹ ትንተና በይናዊ እና መራምራዊ ነው፡፡ ዓለማውም የቋንቋ ዓይነተኛ ተግባር ሥልጣንን መግለጽ መሆኑን ማሳየት ነው፡፡ የሁለቱ ሰበ-ሥልጣናት፣ የሁለቱ ቤተክርስቲያናት አልፎም የሁለቱ መንግሥታት (የኢትዮጵያና የፈረንሳይ) ግንኙት፣ ቅራኔና እርቅ፣ መሠረቱ ሥልጣን ነው፡፡ ቋንቋቸው ይህን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ አልፎም ሃይማኖት የዓለማዊዉ ሥልጣን መጠበቂያና ማስጠበቂያ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ እንደሌለው ያስረዳል፡፡ ቋንቋ የሐሳብ መግለጫ የሚሆነው ሐሳቡ ሥልጣን-አዘል ወይም ሥልጣን-አልባ ሲሆን ነው፡፡ ሥልጣን ዘርፉ እና ደረጃው ብዙ ነው፤ መግለጫው ቋንቋም እንደዚሁ ዓይነቱ ብዙ ነው፡፡ ሰምና ወርቅ አንዱ ነው፡፡

Downloads

Download data is not yet available.

Related articles