የቦረና ኦሮሞ የበኩር ልጅ ስም ስያሜ በዓል ክዋኔ አውድ

  • ደስታ አማረ
Keywords: ቦረና፣ ጉቢሳ፣ ክዋኔ

Abstract

ፎክሎር ህዝቦች በመኖሪያ አካባቢያቸውና በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ሁሉ ሲገናኙ የሚከውኑዋቸው ወጎች፣ እምነቶች፣ ህዝባዊ ጥበቦችንና ሌሎችንም ያካትታል። ከነዚህ አንዱ
የሆነው የስም ስያሜ አንድ ህፃን ከነበረበት ደረጃ ወደ ተከታዩ ወይም ወደ ሌላ ደረጃ መሻገሩንና ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀሉን ያመለክታል። ይህን መሰሉን የደረጃ ሽግግር
የሚያመለክተው ይህ ጥናት በኦሮሚያ ክልል፣ በቦረና ዞን በሚገኘው ቦረና ኦሮሞ የበኩር ልጅ ስም ስያሜ በዓል (ጉቢሳ) ላይ ያተኩራል። ቦረናን ጨምሮ የኦሮሞ ባህልና ወግ በአብዛኛው
ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየው በቃል ነው፡፡ እነዚህ በቃል ያሉ አብዘኛዎቹ ባህልና ወጎች ወይም የፎክሎር ዘርፎች አልተጠኑም። በባህሪ ተለዋዋጭ በመሆናቸው በቃል
ሲያስተላልፉ የነበሩት የህዝቡ ባህላዊ፣ ማህበራዊና መንፈሳዊ እውቀቶችና እሴቶች፣ ይለወጣሉ፣  ይረሳሉ፣ ይጠፋሉ። ስለዚህ አነዚህ አሁን በመከወን ያሉና የመለወጥ እድላቸው ሰፍቶ የሚታዩ
ባህላዊ ክዋኔዎች ተጠንተው በጽሑፍ ቢቀመጡ ነባሩን እውቀት ለትውልድ ማስተላለፍ ይቻላል። በመሆኑም ይህ ሀሳብ ለጥናቱ አነሳሽ ምክንያት ሆኗል። በጥናቱ የቦረና አሮሞዎች የበኩር ልጅ
ስም ስያሜ በዓል ሲያከብሩ ምንምን ክዋኔዎች ይከውናሉ? በየክዋኔዎቹ ምንምን የፎክሎር ዓይነቶች ይቀርባሉ ወይም ይካተታሉ? በየክዋኔዎቹ ውስጥ የህዝቡ ተሳትፎ ምን ይመስላል?
የሚሉት ጥያቄዎች ተመልሰዋል። የጥናቱ ዋና ዓላማ የቦረና ኦሮሞ ማንነትና አተያይ ማሳያ ከሆኑት የባህል ዘርፎች ውስጥ የበኩር ልጅ ስም ስያሜ በዓል ክዋኔዎች በውስጣቸው ከያዙት
የፎክሎር ዓይነቶች፣ ከሚኖራቸው ተምሳሌታዊ ፍችና ከሚያስተላልፉት መልዕክት አንፃር በመግለፅና በመተንተን መዝግቦ ማቆየት ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት በባህል እውቀታቸው
የላቁ ናቸው ተብለው ከሚታወቁት አባቶች ቁልፍ መረጃ አቀባዮች በታላሚ ናሙና ከተመረጡ በኋላ፣ (1)በቃለመጠይቅ (2) በምልከታ እና (3) ተሳትፎ ምልከታ ዘዴዎች መረጃዎቹ
ተሰብስበዋል። ፎክሎር በባህሪው ዘርፈ ብዙ የጥናት ክፍል በመሆኑ የተለያዩ የትንተና አንፃሮች በጥምር መጠቀም ይጠይቃል። ስለሆነም ለዚህ ጥናት መረጃዎች መተንተኛ በዋንኛነት
የተመረጡት የአውድና የክዋኔ የትንተና አንፃሮች ናቸው፡፡ በነዚህ የትንተና አንፃሮች በክዋኔዎች ሂደታዊ አፈፃፀም ባለጉዳዩ የመለየት፣ የሽግግር እና የመቀላቀል ደረጃዎችን ሲሻገር እንዲታይ፣
ክዋኔዎቹና በየክዋኔዎቹ የሚቀርቡት የፎክሎር ዓይነቶች ምንነትና ፍካሬያዊ ትርጓሜያቸውም እንዲሁ ጎልተው እንዲወጡ ተደርገዋል። ባጠቃላይ የበኩር ልጅ ስም ስያሜ በዓል ጉቢሣ
የተለያዩ የፎክሎር ዓይነቶች ማለትም ሥነቃል፣ ቁሳዊ ባህል፣ ሀገረሰባዊ ልማድና ትውን ጥበባትን አካቶ በመያዝ የቦረናን ኦሮሞ እምነት፣ አተያይ፣ ጠንካራ የርስ በርስ ግንኙነት፣ የምጣኔ
ሐብት አገነባብ ዘዴዎችና የባህል ህግጋት ጥበቃ ዘዴዎቹ ጎልተው እንዲታዩ ያደረገ በዓል ነው፡፡

Downloads

Download data is not yet available.

References

Areggaa Hailemicheal. (2005). “A Sociolingustic Approach to the Study of Anyowa Personal Names: A contribution to Socio-Onomastic
Studies in a Nilo-Saharan Language.” Ethiopian Journal of Educational researchers’Association. A.A. Vol. 2 No1, 39-53.
Bouman, R. (1977). Verbal Art as Performance. Rowely Mass: Newbury House.
Dorson, Richard M.(ed) ( 1970). Folklore and Folklife: An Inturduction. Chicago and London: The Unicersity of Chicago Press.
Gennep, Arnold van. (1960). The Rites of Passage. (Translated by Monika B. Vizedom and Gabrielle L.Caffe) London, Western Printing
Service,
Gluckman, Mas. (1962) Ritual of Social Relations (Essays) (ed) Manchester, Manchester Univesity Press.
Oromia, B. (2000). Physical and Socio Economic Profiles of 180 Districts of Oromia Region. Addis Ababa: Bole Printing Press.
Stephens, M. C. (2005). Living Folklore: An Introduction to the Study of People and Their Traditions.Logan, Utah: Utah State University
Press.
Turner, V. (1969). The Ritual Process: Structure and Anti-Strature. Chicago, Aldine.
ያለው እንዳወቀ ሙሉ። (2001) ። የምርምር መሠረታዊ መርሆዎችና አተገባበር።ባህርዳር ዩነቨርስቲ፤ንግድ ማተሚያ ድርጅት።
Published
2018-06-20