የዕድር የሃይማኖት መቻቻል መልኮች በበቆጂ ከተማ

  • ፍሬህይወት ባዩ

Abstract

ዕድር በሀገራችን የተለመደና በተለይ የቀብር ስርዓት እና ተያያዥ ተግባራትን በመተጋገዝ
ለመከወን ተቀራርበው የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በፈቃደኝነት የሚመሰርቱት ባህላዊ ተቋም
ነው። ዕድር በኢትዮጵያ ውስጥ በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ለተመሳሳይ አላማ በየጊዜው የሚቋቋም
ታዋቂ ባህላዊ ተቋም ሲሆን በበቆጂ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ ከ1941 ዓ.ም ጀምሮ የሚታወቅ
ተቋም ነው። በርእሱ የተጠቀሰው የጥናቱ ዋና ዐላማ በበቆጂ ከተማ አስተዳደር የተቋቋሙ
ዕድሮችን ምንነት በመግለጽ የተለያየ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ዕድርተኞች ተቻችለው የአንድ
ዕድር አባል በመሆን የሚኖሩበትን ዘዴ ከፎክሎር ጥናት አኳያ ይተነትናል። መረጃዎቹ በመስክ
በመገኘት በምልከታ፣ በቃለ-መጠይቅ፣ በቡድን ውይይት እና በሰነድ ምርመራ ዘዴ የተሰባሰቡ
ናቸው። በጥናቱ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የክርስትናና የእስልምና ሃይማኖቶች ተከታይ
ማህበረሰቦች ዕድሮችን በጋራ ይመሠርታሉ፡፡ አንድ ዕድር ሲመሰረት የሚቀራረቡ፣ ሰዎች
በፈቃደኝነት ተሰባስበው በተወሰነ ጊዜ በመገናኘት ገንዘብ በማዋጣት የሚመሰርቱት ተቋም ነው።
የሁሉም ዕድሮች ዋና አላማ አባሉ፣ የቅርብ ዘመዱ ፣ ቤተሰቡ ውይም እራሱ በሞት ሲለይ በተለያየ መልኩ
ሀዘንተኛው ለመርዳት ነው፡፡ ሁሉም ዕድሮች በጽሁፍ የሰፈረ መተዳደሪያ ደንብ አላቸው። ደንቦች የያዙት
ዋና ዋና ነጥቦች፡- የዕድሩን አላማ፣ በአባልነት የሚካተቱ ግለሰቦች ማሟላት ስለሚገባቸው መስፈርት፣
የአባላቱ መብትና ግዴታ፣ የዕድሩ አስተዳደር አካል ማንነት፣ መብትና ግዴታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን የያዘ
ነው። በዚሁ መሠረት አንድ የእድሩ አባል ወይም የቅርብ ዘመድ ሲሞት ዕድርተኛው፤ የሟችን
አስከሬን ወደ መቃብር በክብር በመሸኘት ከመቃብር መልስ እስከ ሶስት ቀን የሟችን የቅርብ
ዘመዶች በማጽናናት በጉልበት፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እና በመሳሰሉት ማገዝ ነው። የዕድሮቹ አደረጃጀት
በአንድ ሰፈር የሚኖሩ የመሰረቱት፣ የሰፈር ዕድር ሲባል ይህም የወንዶችና የሴቶች(ወይም የሴቶች
ባልትና) ተብሎይለያያል። በከተማ ውስጥ ነዋሪ የሆነውን ሁሉ የሚያካትተው ትልቁ ዕድር
ይሉታል። በበቆጂ ከተማ ከ1982 ዓም በኋላ የዕድር ክፍፍል የእድሩ አባል በሚከተለው ሃይማኖት
ምክንያት ልዩነት አምጥቷል። ልዩነቱም የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች በአብዛኞቹ ዕድሮች
አባል መሆን አለመቻል ነው። በዕድርተኞች መካከል የሚከወኑ እሴቶች ደግሞ መቻቻል
ከሚያካትታቸው ባሕርያት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የጥናቱ ውጤት እንደሚያመለክተው ተቻችለው የሚኖሩ
የተለያየ ሃይማኖት ተከታዮች እንዳሉት ሁሉ አለመቻቻል የታየባቸው እንዳሉም ይጠቁማል።

Downloads

Download data is not yet available.

References

Alemayehu Seifu,1968; Iddir in Addis Ababa: A sociological study,
Ethiopia Observer.
Alula, Pankhurste (ed), 2003; Iddir participation and Development,
Proceedings of the Ethiopians national Conference.
Dejene, Ardo, 2010; An Informal Insurance Arrangement in Ethiopia;
Saving & development No. 1, xxxIV.
Newman, Jay; The Idea of Religious Tolerance, Journal of American
Philosophical Quarterly,Vol. 15, No. 3, pp 87-195, 1978.
Reat, Ross; 1983; Insiders and Outsiders in the study of Religious
Tradition, Journal of theAmerican Academy of Religion, vol. 51,
No, 3 pp. 459-476.
Shiferaw, Tesfaye; 2002; The role of civil socity Organizations in poverty
alleviation, sustainable development and change: The case of Iddirs
in Akaki, Nazreth and Addis Abeba; Athesis submitted to the school
of graduates of addis Abeba University in partial fulfillment of the
requirement for the degree of the Masters in socal Antropology.
Tomas, Leonard, 2013; Ethiopian Iddirs Mechanisms: The Case study in
Pastorial Communities in Kembata & Wolita; for inter aied
agricultural projects of support to family farming.
ከበቆጂ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የተገኘ ጽሑፍ፤’’ ያልታተ መጥራዝ፤ 1999።
ኪዳነወልድ ክፍሌ። 1948። መፅሐፈ፡ ሰዋሰው፡ ወግስ፡ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ።
አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት።
የበቆጂ ከተማ ሁለተኛ ሸንጎ። 1988። “የመተዳደሪያ ውስጠ ደንብ።”
የበቆጂ ከተማ ምስራቃዊ ሶስተኛ ሸንጎ። 1996 “የመተዳደሪያ ውስጠ ደንብ።”
የበቆጂ ከተማ ስድስተኛ ሸንጎ። 2001። “መተዳደሪያ ደንብ።”
የበቆጂ ከተማ አስረ-ሀንደኛ ሸንጎ። “መተዳደሪያ ደንብ”፤1996
የበቆጂ ከተማ አንደኛ ሸንጎ። 2003። “መተዳደሪያ ደንብ።”
የአማኑኤል ዕድር። 2002። “መተዳደሪያ ደንብ።”
የኪዳነምህረት የሴቶች ባልትና። 1989። “መተዳደሪያ ደንብ።”
የገብርኤል የሴቶች ባልትና። 1998። “መተዳደሪያ ደንብ።”
ፍሬሕይወት ባዩ። 2000። “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ንዋያተ ቅድሳት
ሃይማኖታዊና ፎክሎራዊ ገጽታ።” ለኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሁፍ ትምህርት ክፍል ለ
ኤም ኤ. ዲግሪ ማሟያ፤ በኢትዮጵያ ሥነጽሁፍና ፎክሎር ትምህርት ክፍል፤ አዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ።
Published
2017-12-30