ሀገረ-ሰባዊውን እውቀት መሠረት ያደረጉ ንዋየ ቅድሳት ፋይዳ እና ተግዳሮቶቹ

  • ፍሬህይወት ባዩ

Abstract

በዚህ ጥናት ንዋየ ቅድሳት የተባሉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን(የኢ.ኦ.ተ.ቤ)
የአምልኮ ሥርዓት የሚፈጸምባቸው እቃዎች ናቸው፡፡ እቃዎቹ ለአገልግሎት ከመዋላቸው በፊት
የሚደረግላቸው የጸሎት ሥርዓትና የሚቀቡት ቅብዐ ቅዱስ ከመሰል ቁሶች ለይቷቸው ንዋየ
ቅድሳት የሚለውን ስም አሰጥቷቸዋል። የጥናቱ ማእቀፍ የፎክሎር የጥናት መስክ
ከሚያተኩርባቸው መካከል ቁሳዊ ባሀል ላይ ያተኩራል። የኢ.ኦ.ተ.ቤ ንዋያተ ቅድሳት መካከል
ሀገረ-ሰባዊ እውቀትን መሠረት ያደረጉ እንደሆኑ በማሳየት ለሀገር በቀል እውቀት ያላቸውን ፋይዳ
ሊያሳጣቸው የሚችለውን ተግዳሮቶች መጠቆም የጥናቱ ዋና አላማ ነው። የጥናቱ አስፈላጊነት
ንዋየ ቅድሳት ተግባራቸው ሃይማኖታዊ ቢሆንም ሀገረ-ሰባዊ እውቀትን መሰረት ያደረጉ
መሆናቸው የተለያዩ ጠቀሜታዎች እንዳላቸው ያሳያል። አጥኚዋ ቀደም ሲል ንዋየ ቅድሳት ላይ
ጥናት በማድረግ በየጊዜው የሚታይባቸውን ለውጦች በማስተዋል ከጊዜ ወደ ጊዜ ተግዳሮቶች
መታየታቸው ተጨማሪ ጥናት ለማድረግ መነሻ ምክንያት ሆኗታል። በጥናቱ ውጤት
ሀገረሰባዊውን እውቀት መሰረት አድርገው በመሰራት ላይ የሚገኙትን ለማሳያ ምሳሌ በማቅረብ
እንደ ሀገር ሀብትነታቸው ያሉ ተግዳሮቶች ተጠቁመዋል። ንዋየ ቅድሳት የሚባሉት የኢ.ኦ.ተ.ቤ
ለአምልኮ ተግባር የምትገለገልበት ሕንጻ ቤተ-ክርስቲያኑን ጨምሮ በህንጻ ቤተ-ክርስቲያን የውስጥ
ክፍሎች ለአምልኮ ተግባር የሚያገለግሉ ናቸው። የኢ.ኦ.ተ.ቤ ንዋየ ቅድሳት በቀደሙት ዘመናት
ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ባለሙያ እና በአካባቢው በሚገኙ ቁሶች የሚሰራ ነበር። ከጊዜ
ወደጊዜ የሚሰሩበት ጥሬ እቃ በከፊል ከውጭ ሀገራት በሚመጡ ጥሬ እቃዎች እየተተኩ
እንዲሁም በውጭ ሀገራት ተሰርተው የሚመጡ ናቸው። ቁሶቹን የመስራት እውቀት በውጭ
ሀገራት በሚገቡ ቁሶች እየተተኩ መሆን ከተግዳሮቶቹ ዋንኛው ነው። ይህ ተግዳሮት እንደ ሀገር
ለዘመናት የኖረውን ሀገር በቀል እውቀት ማጣትን ያስከትላል። ጥሬ እቃዎቹንም ሆነ የተሰሩትን
ከውጭ ሀገራት በማምጣት ባህላዊውንና ሀገር በቀሉን እውቀት ከማዘመን ይልቅ እንዲቀጭጭ
አንዳንዶቹም ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ ምክንያትእየሆነ መጥቷል። በጥናቱ ለተነሱት ተግዳሮቶች
እንደ መፍትሄ ሀሳብ የተጠቆመው የኢ.ኦ.ተ.ቤ ንዋየ ቅድሳትን ለመስራት የሚያስችል ትልቅ
ኢንዱስትሪ ብታቋቁም ሃይማኖታዊ ደንቡን የጠበቁ ንዋየ ቅድሳትን ታገኛለች፣ ለምእመናኑ የስራ
መስክ ትከፍታለች እንዲሁም ለባህል ኢንዱስትሪው ሀገረሰባዊው የእውቀት ሽግግር እንዳይገታ
ትታደገዋለች።

Downloads

Download data is not yet available.

References

ሀብተማርያም ወርቅነህ። 1963። ጥንታዊ የኢትዮጵያ ትምህርት። አዲስ አበባ ብርሃንና ሰላም
ቀዳማዊ/ሥላሴ ማተሚያ ቤት።
ሉሌ መልአኩ:: 1986:: የቤተክርስቲያን ታሪክ:: አዲስ አበባ ትንሣኤ ማተሚያ ድርጅት።
ነጋሽ በቀለ። 1988። “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተዳደርና ትምህርት አጭር
ጥናታዊ ጽሁፍ።” ያልታተመ።
አስኳል አማረ። 1994።ንዋየ ቅድሳትን ለአገልግሎት ሊያውሏቸው ይገባልን። ሐመር። አዲስ አበባ ብራና
ማተሚያ ቤት።
ዐብይ ፍትህ አወቅ። 1963። “ንዋየ ቅድሳት”። ዲማጽ (ለኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሁፍ ትምህርት
ክፍል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ።
ኪዳነ ወልድ ክፍሌ። 1948። መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ። አዲስ አበባ።
አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት።
ክንፈ ገብርኤል አልታዬ። 1992። ሥርዓተ ቤተ-ክርስቲያን። አዲስ አበባ። ትንሣኤ ማተሚያ ድርጅት።
ክንፈ ገብርኤልና ጌታቸው። 1998። ሥርዓተ ቤተክርስቲያን:: አዲስ በባ ትንሣኤ ማተሚያ ቤት።ኢትዮጵያ
መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ። 1980። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሀዲስ ኪዳን መጻህፍት)።
አዲስአበባ። ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን። 1994። የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን ትላንትና ዛሬና
ነገ። አዲስ አበባ ሜጋ ማተሚያ ኢንተርፕራይዝ።
ያሬድ ገ/መድህን። 1996። ኖኀተ ሰማይ። አዲስ አበባ። ሜጋ ማተሚያ ኢንተርኘራይዝ።
ፈቃደ አዘዘ። 1991። የሥነ-ቃል መምሪያ። አዲስ አበባ። ቦሌ ማተሚያ ድርጅት::
ፍሬሕይወት ባዩ። 2000። “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ዋያተ ቅድሳት ሃይማኖታዊና
ፎክሎራዊ ገጽታ”ለኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሁፍ ትምህርት ክፍል ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ
በኢትዮጵያ ሥነጽሁፍና ፎክሎር። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ።
Published
2017-12-30