የሰብአዊነት አሣሣል በዐፄ ሱስንዮስ ዜና መዋዕል እና በበዓሉ ግርማ የቀይ ኮከብ ጥሪ ውስጥ

  • Taye Assefa Ethiopian Academy of Sciences

Abstract

የአማርኛ ዘመናዊ ልቦለድ እድገት ከአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ልብ ወለድ ታሪክ (ጦብያ) በ1900 ዓ/ም መታተም በኋላ ጎላ ያለ የጭብጥም የቅርጽም ለውጥ አስመዝግቧል፡፡ በርካታዎቹ የዘመናዊነት ገጽታዎቹም የዚህን የሥነ ጽሑፍ ዘውግ አታቾች ትኩረት በተለያየ ደረጃ ስበዋል፡፡ ሆኖም፣ ለአማርኛው ልቦለድ የግእዙ ሥነ ጽሑፍ መሠረትነት ወይም ይህ የልቦለድ ዘውግ በእድገት ግሥጋሴውም ላይ ቢሆን ከግእዙ ጋር በምን ሁኔታ እንደሚወራረስ ለማሳየት የሚገባውን ያህል በተመራማሪዎች አልተፈተሸም፡፡ ይህ ጽሑፍ ለአብነት የዐፄ ሱስንዮስን ዜና መዋዕል (ከግእዝ ወደ አማርኛ የተተረጎመ) ከበዓሉ ግርማ የቀይ ኮከብ ጥሪ ጋር በማነጻጸር ከሥነ ምግባራዊ ሰብዓዊነት ጭብጥ አተራረክ አንጻር ሁለቱ ያላቸውን ተመሳስሎና ልዩነት ለማሳየት ይሞክራል፡፡ ሁለቱን ድርሰቶች ለማነጻጸር መንደርደሪያው ሁለቱም ትርክ መሆናቸው፣ የሚሥሉት እውነታ በምናብ የተዋዛ መሆኑ፣ ታሪካቸው በተወሰነ ደረጃ በተመሳሳይ ፖለቲካዊ መርሖች የተቃኘ መሆኑና የሁለቱም ደራስያን የፖለቲካ ሹመኞች መሆናቸው ነው፡፡ ጽሑፉ ለአምባገነን አገዛዝ የቅርብ ባለሟል የሆነ ደራሲ ድርሰቱን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ማዋሉ ከጥንት የተወረሰ የድርሰት ባህል መሆኑን በአንድ በኩል ቢያረጋግጥም በሌላ በኩል ግን የኅሊና ሙግት ያለበት ደራሲ የፕሮፓጋንዳውን ማርከሻ በተዘዋዋሪ ለአንባቢው የሚያቀርብበት ሰምና ወርቅ ቅኔ መሰል የአተራረክ ስልት እንዳለውም ከዜና መዋዕሉ ማስረጃዎችን በመጠቃቀስ ያሳያል፡፡

Downloads

Download data is not yet available.

References

መስፍን ሀብተ ማርያም፡፡ 1972 ዓ/ም፡፡ ሥነ ጽሑፍ ከአብዮት ፍንዳታ ወዲህ፤ የቀይ ኮከብ ጥሪ (ግምገማ)፤ የካቲት፤ 3ኛ ዓመት፣ ቁ. 5፣ ገጽ 26-27፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ፤ 2000 ዓ/ም፤ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት፤ አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፡፡
በዓሉ ግርማ፤1972 ዓ/ም፤ የቀይ ኮከብ ጥሪ፤ አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ መጻሕፍት ድርጅት፡፡
_____፤ 1975 ዓ/ም፤ ኦሮማይ፤ አዲስ አበባ፤ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት፡፡
ተሰማ ሀብተሚካኤል፤ 2002 ዓ/ም፤ ከሳቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፤ አዲስ አበባ፡፡
ተክለ ኢየሱስ ዋቅጅራ (አለቃ)፤ 2002 ዓ/ም፤ የኢትዮጵያ ታሪክ፤ ሐተታ በሥርግው ገላው፤ አዲስ አበባ፡፡
ተክለ ጻድቅ መኩሪያ፤ 1953 ዓ/ም፤ የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ልብነ ድንግል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ፤ አዲስ አበባ፡፡
አንዳርጋቸው አሰግድ፣ 1992 ዓ/ም፤ በአጭር የተቀጨው ረጅም ጉዞ፤ መኢሶን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ውስጥ፤ አዲስ አበባ፡፡
አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፤ 1901 ዓ/ም፤ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ፤ ሮማ፡፡
እንዳለጌታ ከበደ፤ 2008 ዓ/ም፤ በዓሉ ግርማ፤ ሕይወቱና ሥራዎቹ፤ አዲስ አበባ፡፡

ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ 1948 ዓ/ም፣ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ አዲስ አበባ፡፡
ዓለሙ ኃይሌ (ተርጓሚ)፤ 1998 ዓ/ም፡፡ የአፄ ገላውዴዎስ ዜና መዋዕል፤ አማርኛና ግእዝ፤ አዲስ አበባ፤ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን፡፡
_____፤ 1999 ዓ/ም፤ የአፄ ሠርጸ ድንግል ዜና መዋዕል፤ ግእዝና አማርኛ፤ አዲስ አበባ፤ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን፡፡
_____፤ 2005 ዓ/ም፤ የኢትዮጵያ ታሪክ (1597-1625)፤ የአፄ ሱስንዮስ ዜና መዋዕል፤ አዲስ አበባ፤ ሲራክ አሳታሚ ድርጀት፡፡
_____፤ 2006 ዓ/ም፤ የዐፄ በካፋ ታሪከ ነገሥት፤ አዲስ አበባ፤ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን፡፡
ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ፤ 1904 ዓ/ም፤ “አጤ ምኒልክና ኢትዮጵያ”፤ ጳውሎስ መናመኖ ባዘጋጀው ብርሃን ይኹን ውስጥ፡፡
ገነት አየለ አንበሴ፤ 2000 ዓ/ም፤ የሌተናንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያም ትዝታዎች፤ 2ኛ እትም፤ አዲስ አበባ፡፡
ጌታቸው ኃይሌ፤ 1993 ዓ/ም፤ ባሕረ ሐሳብ፤ የዘመን ቆጠራ ቅርሳችን ከታሪክ ማስታወሻ ጋራ፤ ኮሌጅቪል/ሚነሶታ፡፡
ፍትሐ ነገሥት፤ ንባቡና ትርጓሜው፤ 1993 ዓ/ም፤ አዲስ አበባ፤ ትንሣኤ የመጻሕፍት ማሳተሚያ ድርጅት፡፡
Boavida, Isabel, Hervé Pennec and Manuel João Ramos, eds. 2011. Pedro Páez’s History of Ethiopia, 1622. Translated by Christopher J. Tribe. Vol. II. London: The Hakluyt Society.
Chernetsov, Sevir. 1988. “Medieval Ethiopian historiographers and their methods”, Proceedings of the Ninth International Conference of Ethiopian Studies, edited by An. A. Gromyko, 191-200. Vol. 5. Moscow: Nauka Publishers.
_____. 1994. “The crisis of Ethiopian official historiography and its consequences in the 18th century”, Proceedings of the Eleventh International Conference of Ethiopian Studies, edited by Bahru Zewde, Richard Pankhurst and Taddese Beyene, 87-101. Vol. I. Addis Ababa: Institute of Ethiopian Studies (AAU).
Genette, Gérard. 1980. Narrative discourse. Trans. by Jane E. Lewin. Oxford: Basil Blackwell.
Getachew Sahle Mariam. 1985. A study of some major characteristics and themes in Post-Revolution Amharic novels, 1974-82. M.A. Thesis, AAU, Addis Ababa.
Kapeliuk, Olga. 1982. A novel about the Red Terror. Northeast African Studies 4, no. 2: 57-64.
Michael Fiqremariam. 2009. A study of the influence of Marxism on Bealu Girma’s three novels: Haddis, Yekey Kokeb Tiri, and Derasiw. M.A. Thesis, AAU, Addis Ababa.
Rimmon-Kenan, Shlomith. 1983. Narrative fiction: Contemporary poetics. London and New York: Methuen.
Sileshi Tuji. 2007. Red-Terror inspired prose fiction: Character and thematic issues. M.A. Thesis, AAU, Addis Ababa.
Taye Assefa. 1989. “The Post-Revolution Amharic novel (1966-1975 E.C).” In Proceedings of the Eighth International Conference of Ethiopian Studies, edited by Taddese Beyene, 591-606. Vol. 2. Addis Ababa: Institute of Ethiopian Studies.
Toubkis, Oleg Dimitri. 2004. “Je deviendrai roi sur tout le pays d'Ethiopie”. Royauté et écriture de l'histoire dans l'Ethiopie chrétienne (XVme-XVIIme siècles). Thèse pourle doctorat en histoire, Université de Paris 1 Panthéon-Sorbonne. Vol. I.
Toubkis, O. Dimitri. 2010. “Täklä Sellasé”, Encyclopaedia Aethiopica. Vol. 4. Wiesbaden: Harrassowitz Verlag.
Published
2021-09-22