በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት እና መዛግብት

  • Mengistu Gobezie Lecturer of Archaeology and Heritage Management , Addis Ababa University

Abstract

ኢትዮጵያ የበርካታ ባህላዊ እና ተፈጥሯዊ ቅርሶች ባለቤት ናት፡፡ ብዙዎቹ የአገሪቱ ባህላዊ ቅርሶች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይዞታ ሥር የሚገኙ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በርከት ያሉ ባህላዊ ቅርሶችን በዓለም አቀፍ ቅርስነት በማስመዝገብ በአፍሪካ በግንባር ቀደምነት ትጠቀሳለች፡፡ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስ  እና ባህል ድርጅት/UNESCO/ ከተመዘገቡት ስምንት ዓለም አቀፍ ቅርሶች ውስጥ ሰባቱ ባህላዊ ቅርሶች ናቸው፡፡ ይኹንና ከሰባቱ ባህላዊ ቅርሶች ሌላ አገራችን ዐሥራ ሁለት የሥነ ጽሑፍ ሀብቶችን በዓለም ቅርስነት አስመዝግባለች፡፡ እነዚህ ቅርሶች የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መምህራን እና ሊቃውንት ብራና ፍቀው፣ ብዕር ቀርጸው እና ቀለም በጥብጠው ለትውልድ ያበረከቷቸው የብራና መጻሕፍት እና መዛግብት ናቸው፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ዓለምአቀፍ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶቻችንን ማስተዋወቅ እና ጠንክሮ መሥራት ከተቻለ ሌሎች በርካታ ሀብቶቻችንን በዓለም ቅርስነት ማስመዝገብ እና ተጠቃሚ መኾን እንደሚቻል ማመልከት ነው፡፡

Downloads

Download data is not yet available.