Mariology in the E.O.T.C Tradition: Special Emphasis on Dǝrsanä Ṣǝyon

  • Amsalu Tefera

Abstract

አጠቃሎ

በክርስትናው ምሂር ግንባር ቀደም ከሆኑት አንዱና ዋናው «ነገረ ማርያም» ነው። በዚህም ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዜና ሕይወት፣ አምላክን በኅቱም ድንግልና ስለመውለዷ፣ ስለ ክብረ ቅድስት ድንግል፣ ወዘተ... ይጻፋል፣ ይተረጎማል፣ ትምህርት ይሰጣል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ይህን መሠረታዊ ትምህርት ጠብቀው ከያዙትና በስፋትም ከሚያስተምሩት ቀዳሚዋ ናት። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችንን ክብርና ልዕልና የሚያስረዱ በርካታ መጻሕፍት ይገኛሉ። ለምሳሌ መጽሐፈ ልደታ፣ ነገረ ማርያም፣ መጽሐፈ ዕረፍታ፣ ውዳሴ ማርያም፣ ተአምረ ማርያም፣ ቅዳሴ ማርያም፣ ድርሳነ ማርያም፣ ድርሳነ ጽዮን፣ መዝሙረ ድንግል፣ መልክአ ማርያም፣ አርጋኖነ ውዳሴ፤ ወዘተ... ግንባር ቀደምት ናቸው። የእነዚህና ሌሎች ዋና ዋና መጻሕፍት ዝርዝር እና የያዙት ጭብጥ፣ ስለ እመቤታችን ክብር ጠቅለል ባለ መልኩ በዚህ ጽሑፍ የመጀመሪያ ሦስት ክፍሎች ውስጥ ተዳሰዋል። በእግዚአብሔር ጣቶች ስለተጻፉት ሁለቱ ጽላትና እና ለሙሴ ስለተሰጠችው ታቦተ ጽዮን ክብር እንዲሁም ስለ እመቤታችን አማናዊ ጽዮንነት በስፋት የሚዘረዝረውና ስለ ክብረ ድንግል ከሚያስረዱት መጽሐፍት አንዱ የሆነው ድርሳነ ጽዮን ነው። የዚህ ጽሑፍ አራተኛ ክፍል በድርሳነ ጽዮን ውስጥ የተገለጹትን ትምህርቶች ማለትም ስለ እመቤታችን ጽዮንነት፣ ሰማያዊ ክብር፣ ልዩ ልዩ ሕብርና ምሳሌያት የሚገልጹትን ምንባባት በመዘርዘር ምሥጢራቸውን ያራቅቃል።    

 

 

Downloads

Download data is not yet available.
Published
2012-08-20