Change and Survival in the Oral Poetry of the Tämari

  • Meseret Kebede

Abstract

የአብነት ተማሪ ሥነ ቃል -  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በቃል የሚፈጠር፣ የሚከወን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍና የሚጠበቅ የሥነ ቃል ዓይነት - የአብነት ተማሪዎችና ሊቃውንተ ቤተክርስትያን የአብነት ትምህርት ቤቶችንና የአብነት ትምህርትን በሞትና በተለያዩ ምክንያቶች እየተዉ በመሄዳቸው የአብነት ትምህርት ቤትና የአብነት ትምህርት ለመጥፋት መድረሳቸውን እንዲሁም የቤተክርስትያኒቱ መንፈሳዊ አገልግሎት አደጋ ላይ መውደቁን ይጠቁማል፡፡ ቃል ግጥሞቹ ቤተክርስትያኒቱ የምትሠጠውን አገልግሎት ለማሻሻልና የአብነት ትምህርትንና ትምህርት ቤትን ሕልውና ለማርዘም ለውጥ እንደሚያስፈልግ ይሰብካሉ፡፡ ተማሪዎች ከረሀብና ከእርዛት፣ ከቃል ትምህርትና እንደ መምህራቸው ለመሆን ከሚያደርጉት  ጥረት ጋር ሲታገሉ ቆይተው ትምህርታቸውን ቢያጠናቅቁም የአብነት ትምህርት ቤት በመክፈት ደቀ መዛሙርት ማፍራት፣ በቤተክርስትያኒቱ የተለያዩ መዋቅሮች ውስጥ በመግባት ማገልገልና ራሳቸውን የሚችሉበት ገቢ ማግኘት እንዲሁም ከኅብረተሰቡ ክብርን ማግኘት አልቻሉም፡፡ ቃል ግጥሞቹ ቤተክርስቲያን የትምህርቱን ዕሴት ከፍ በማድረግ ወደ ተቋሙ የሚገቡ ተማሪዎችን መሣብ የሚቻልበትን አቅም መፍጠር እንደሚገባ ያሳስባሉ፡፡ 

 

Downloads

Download data is not yet available.
Published
2012-08-20