Role of Trees in Church compound for Carbon Emission Reduction

  • Tulu Tolla, Mekuria Argaw and Zewdu Eshetu

Abstract

ደን የአየር ለውጥን ለመከላከልና የካርበን ክምችትን ለመቀነስ ከየትኛውም ሥነ ምሕዳር ክፍል በላይ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ የሚገኙ ደኖች በሌሎቹ የአገሪቱ ክፍል ከሚገኙ የደን ዓይነት በተሻለ ተጠብቀው እና ተንከባክበው ይገኛሉ፡፡ የዚህ ጥናት አጠቃላይ ሁኔታ የሚያተኩረው በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ የሚገኙ ደኖች ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን ካርበን ለመቀነስ እና የዓለም ሙቀት መጨመርን በመከላከል ዙሪያ ያላቸውን አስተዋጽዎ ለመመልከት ሲሆን፤ በዚሁ መሠረት አዲስ አበባ በሚገኙ ሰባት አድባራትና ገዳማት ላይ ይህ ጥናት ተደርጓል፡፡ በሰባቱ የጥናት ቦታዎች የሚገኙ የዛፍ ዝርያዎች ክብ መጠናቸው (Diameter at Brest height)  ከ10 ሴ.ሜ በላይ የሆኑት የተካተቱ ሲሆን የእያንዳንዱ ዛፍ ክብ መጠን፣ ቁመት (height)፣ መነሻ ርዝመት (Basal height) እና የቅርንጫፎቹ ርዝመት (crown height) ተለክቷል፡፡ በዚህ ልኬት ላይ በመመርኮዝ በቆመው ዛፍ ከመሬት በላይ ባለው አካሉ  (Above Ground Biomass) እና ከመሬት በታች ባለው አካሉ (below ground biomass) ውስጥ የሚገኘው ካርበን ልኬታ ተሰልቷል፡፡ በቆመው ዛፍ ከመሬት በላይ ባለው ደረቅ ክብደቱ ውስጥ ያለውን ካርበን ለማወቅ አሎሜትሪክ ሞዴል (allometric model) የተጠቀመ ሲሆን ከመሬት በታች ባለው ደረቅ  ክብደት ውስጥ የሚገኘውን ካርበን ለማወቅ ከመሬት በታች እና ከመሬት በላይ ያለውን ክፍልፋይ (Below Ground to Above Biomass ratio) ተጠቅሟል፡፡ በዚሁ መሠረት የጥናቱ ውጤት የሚያሳየው ክብ መጠናቸው ከ10 ሴ.ሜ በላይ የሚሆኑ 1519 ዛፎች የተገኙ ሲሆን በነዚህ ዛፎች ከመሬት በላይና ከመሬት በታች ደረቅ ክብደታቸው ውስጥ የካርበን ልክ በአማካይ ከ129.85+154.11 እና 25.97+30.82ቶን በሄክታር ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በአማካይ እያንዳንዱ ዛፍ 0.6+0.69 ቶን ካርበን እንደተከማቸ ለማወቅ ተችለዋል፡፡ ከዚህ ጥናት ለመረዳት እንደተቻለው የአየር ለውጥን ለመቀነስ በሚደረገው የደን ማልማትና መንከባከብ አቅጣጫ የቤተ ክርስቲያን ደኖች ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን ካርበን በመቀነስ (carbon emission reduction) እና በሚገኝበት ቦታ ብዝኃ ሕይወትን በመጠበቅ (insitu biodiversity conservation) ዙሪያ የጎላ አስተዋጽዎ እንደሚያደርጉ ያመለክታል፡፡

 

Downloads

Download data is not yet available.
Published
2012-08-20