The Cross in Ethiopia: Decoding the Symbolisms in the Christian Traditions

  • Alelign Aschale

Abstract

 

የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች መስቀል የቅዱስ ኃይል፣ የመከታ፣ የመሥዋዕትነት፣ የድኅነትና የዘላለማዊነት ዐርማ መሆኑን በጽኑ ያምናሉ፡፡ በኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ታሪክና ወግ መሠረት መስቀል ከፍተኛ ቦታ አለው፡፡ ምክንያቱም በመስቀል መንፈሳዊ ይግባኝ መጠየቅና የእግዚአብሔርን መንግሥት መውረስ ይቻላል፡፡ ለዚኽ የኢትዮጵያ መስቀል የተለያዩ ምስጢራዊ ትዕምርቶችን የያዘ ነው፡፡ በዚኽ ጥናት ውስጥ የጥልቅ ትእምርታዊ ትንተና (Critical Semiotic Analysis) ምርምር ዘዴን በመጠቀም ከ፪፻ በላይ የሚኾኑ የኢትዮጵያ የመስቀል ዐይነቶችን ለመመርመር ተሞክሯል፡፡ በጥናቱ መሠረት የልመና ማቅረቢያ፣ የድኅነት ማግኛ፣ ወዘተ…ትእምርቶች ተጣምረው ይገኛሉ፡፡ ከሌሎች በላቀ መልኩ የ“እንስሳት”፣ የዕፅዋት፣ የቋጠሮ ሥራዎችና የተለያዩ ሥነ ቅርጾች በብዛት ይገኛሉ፡፡ እንዲኹም እያንዳንዱ ትእምርት በተለያየ መልክ፣ ቦታ፣ አቀማመጥና መጠን ይገኛል፡፡ ይኽም መንፈሳዊ መስተጋብርን ለማስማማት ስለሚረዳ ሰይጣንን (ዲያብሎስን) ድል ለመንሣት ከማንኛውም ዐይነት መጥፎ ወጥመድ ለማምለጥና ከሞት ለመዳን ይረዳል፡፡ በእጅ መሳይ ትእምርት ወደ ላይ በመዘርጋት መደገፍ (ማቀፍ) የታላላቅ መስቀሎች ልዩ ባሕርይ ሲኾን ይኽም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ጥልቅ ፍቅርና የግንኙነት ኃይል ያመለክታል፡፡ በእጅ መስቀሎች ላይ ደግሞ በመንግሥተ ሰማይ በመሬትና በሰው መካከል ያለውን ምስጢራዊና ተዛማጅ የግንኙነት ኃይል ያሳያል። ለእነዚኽና ተዛማጅ ትእምርቶች ዋነኛው ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ ሲኾን ተወራራሽ ትርጓሜዎችም ኹነኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ ኾኖም ግን የመስቀል ሠራተኞች ግላዊ ጥበብ፣ ክህሎትና ሃይማኖታዊ ዕውቀት፣ የቀሳውስት፣ ዲያቆናትና መስቀል አሠሪዎች አስተምህሮና ትእዛዝ የተለያዩ ምስጢራዊ ትእምርቶች በመስቀል ላይ እንዲቀመጡ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በኸኽ ጥናት ውስጥ ሌሎች ተዛማጅ ግኝቶችም ተመርምረዋል፡፡

Downloads

Download data is not yet available.
Published
2017-08-10