የጠበል ፎክሎራዊ ገጽታ በጨፋ/በጎንዴ ጠበል ማሳያነት

  • ፍሬህይወት ባዩ

Abstract

አጠቃሎ

ይህ ጥናት ያተኮረው በጨፋ ጠበል ፎክሎራዊ ክዋኔ ላይ ነው። በተለምዶ ጠበሉ የፈለቀበት አካባቢ በሚጠራበት ስም የጨፋ/የጎንዴ ጠበል በመባል ይታወቃል። በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ይገኛል። ጥናቱ የፎክሎርን የጥናት መስክ መሠረት አድርጎ ከ2005 እስከ 2008 ዓ.ም ድረስ በተለያየ ጊዜ በቃለ-መጠይቅና በምልከታ በተገኘ መረጃ ላይ ተመሥርቶ የተከናወነ ነው። የጠበሉ መፍለቅ ለጨፋ መድሀኒዓለም ደብረቁስቋም፣ ቅድስት ማርያም ወሰሎሜ አንድነት ገዳም መመሥረት ምክንያት ሆኗል። በጠበሉ የሚገለገሉት የእስልምናና የኢ.ኦ.ተ.ቤ ሃይማኖት ተከታዮች ሲሆኑ ጠበል ለመነከርና ለመጠጣት የሚመጡት የጤና መታወክ የደረሰባቸው ግለሰቦች ናቸው። የውሀ ምንጩ ከተራ ውሃነት ወደ ተቀደሰ ውሃነት የተቀየረው በራእይ አማካይነት ነው። ራእይ አንዱ የሚት ጥናት ትኩረት ነው። ከራእዩ ተረኩ ተገነባ። ተረኩ እምነትን መሠረተ። ራእዩ ሁለት ቤተ-ክርስቲያን ተሰርቶ ገዳም እንዲገደም ምክንያት ሆነ። ይህ ራእይ እንዲሁም ትረካ ለአማኙ ማህበረሰብ የተቀደሰ ትረካ ይሆናል። ለማያምንበት ደግሞ እንደ አተያዩ የተለያየ ትርጉም ወይም ሀቲት ሊሰጠው ይችላል። ትረካው በቃል ከአንዱ ወደ ሌላው እየተላለፈ እምነቱ እየሰፋ የጠበል ተጠማቂው ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ከሀያ ሶስት አመት በላይ ሆኖታል። ተጠማቂዎቹ ለጠበል አጠማመቁ በልማድ ብቻ ደንብ አውጥተውለታል። እያንዳንዱ የጠበሉ ተጠማቂ ስለ ጠበሉ በተለይ ከህመሙ ስለማዳኑ የሚተርካቸው ግለ ታሪኩ “ጠበል ያድናል” የሚለውን እምነት የሚተክሉ ናቸው። በጥቅሉ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ በጠበል ምክንያት የተገናኙ ማህበረሰቦች እምነት፣ አተያይ፣ ሃይማኖት ያልገደበው ማህበራዊ መስተጋብር  የሚታይበት ነው።  

DB Error: MySQL server has gone away

DB Error: MySQL server has gone away