Author Guidelines
ሀ. የጥናታዊ ጽሑፉ ርእስ
ለ. የጥናት ጽሑፉን ያየው/የገመገመው ሰው ስም፣ ማዕረግ እና አድራሻ
ሐ. የጥናት ጽሑፉ ለገምጋሚው የተሰጠበት ቀን
መ. የገምጋሚው ግብረ-መልስ ለጥናት ማእከሉ ገቢ የተደረገበት ቀን
ሠ. የጥናት ጽሑፉ ሊገመገምባቸው የሚችሉ መሥፈርቶች
፩. የጥናት ጽሑፉ ርእስ በጥናት ዘገባው ውስጥ የተዳሠሠውን ይዘት በትክክል ያንጸባርቃል?
፪. አጠቃሎው የጥናት ጽሑፉን ዐላማ፣ ዘዴ፣ ቅደም ተከተል፣ ዐበይት ግኝቶችና የመፍትሔ ሐሳቦች በግልጽና በአጭሩ ያብራራል?
፫. የጥናት ጽሑፉ ዐላማዎች፣ መሠረታዊ ጥያቄዎችና የጥናቱ መላምቶች በግልጽና በዝርዝር ተገልጸዋል?
፬. ጥናቱ ያነሳው ርእሰ ጉዳይ አንዳች ፋይዳ ያለውና ሊመረምሩት የሚገባ ነውን? ማለትም እንዲሁ ለሐሳባዊ/ሀልዮታዊ መራቀቅ ብቻ የሚያገለግል ነው ወይንስ አንዳች ተግባራዊ ዋጋ (ጠቀሜታ) አለው? ጥቅሞቹስ በዝርዝር፥ በግልጽና በትክክል ተገልጽዋል?
፭. ሥራው በቂና በትክክል የተደራጀ ተዛማጅ ክለሳ ድርሳናትን ይዟል? የተጠቀመባቸውን ሥራዎችስ በአግባቡ ምንጫቸውን ጠቅሷል? ተመራማሪው ከሚሠራው ጥናት ጭብጥ ጋር የበለጠ አግባብነት ያላቸውንና ሊገኙ የሚችሉ ምንጮችን በበቂ ሁኔታ ለመዳሠሥ ሞክሯልን?
፮. የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎቹ፣ አካሄዶቹ (ቅደም ተከተሎቹ)ና መሣሪያዎቹ በእርግጥ አስተማማኝ ናቸው? በአግባቡና በበቂ መጠን ተገልጸዋል?
፯. ለጥናቱ የተወሰዱ ናሙናዎችስ በትክክል ተገልጸዋል/ተብራርተዋል? የናሙና መምረጫ መሥፈርቱስ እውነተኛና አግባብ ነው?
፰. የቀረበው መረጃ የጥናቱን መሠረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ወይም ዝርዝር ዐላማዎች ለማሳካት በቂና አግባብነት ያለው ነውን?
፱. የተመረጡት የመረጃ መተንተኛ ዘዴዎች ለተሰበሰበው መረጃ ባሕርይ ተስማሚ ወይም አግባብነት ያላቸው ናቸውን?
፲. ማጠቃለያና መደምደሚያዎቹ ከጥናቱ ዐበይትና ንኡሳን ዐላማዎች ጋር አብረው ይሄዳሉ/የተሰናሰሉ ናቸው?
፲፩. ጥናታዊ ጽሑፉ በርእሰ ጉዳዩ የተነሣውን መሠረታዊ ችግር ለመፍታት የሚያስችል አግባብነት ያለውና ሊተገበር የሚችል የመፍትሔ ሐሳብ ይዟል?
፲፪. በአጠቃላይ የጥናት ጽሑፉ አቀራረብ ግልጽ፣ አጭርና የማያሻማ ነው? የጽሑፉ ክፍሎች የርስበርስ ዝምድና፣ ግንኙነት፣ ተለጣጣቂነትና አንድነት ትክክል ነው?
ረ. የገምጋሚው አጠቃላይ የፍተሻ ውጤት
አጠቃላይ በማንኛውም ሳይንሳዊ መመዘኛ የጥናት ወረቀቱ (ከፊት ለፊቱ የ ምልክት በማድረግ ያመልክቱ)
ጥናትና ምርምር መጽሔት ላይ ሊታተም የሚችል ነው _
መጠነኛ ማስተካከያ በጥናትና ምርምር መጽሔት ላይ ሊታተም የሚችል ነው _
በከፍተኛ ማስተካከያ በጥናትና ምርምር መጽሔት ላይ ሊታተም የሚችል ነው _
ፍም በጥናትና ምርምር መጽሔት ላይ ሊታተም የሚችል አይደለም _
ሰ. የገምጋሚው አስተያየት፦ እባክዎ የጽሑፉን ጠንካራና ደካማ ጎን እና በርእሰ ጉዳዩ ውስጥ መነሳት ያለባቸው ዋናዋና ነጥቦች በትክክልና በአግባቡ መነሣታቸውንና ጽሑፉ ለመጽሔት የሚገባ መሆን አለመሆኑን ይግለጹ (አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ ገጽ ይጠቀሙ)።