Articles
የቀብርና ሀዘን ሥርዓት ክዋኔዎች በወሊሶ ሊበን ኦሮሞ
- Journal ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
- Issue Vol 26 No 2 (2017): ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
- Published
- ISSN 2222-6028
Abstract
ይህ ጥናት በወሊሶ ሊበን ኦሮሞ የቀብርና የሀዘን ሥርዓት ላይ ያተኩራል። በጥናቱ አካባቢ ሞት
ከተከሰተበት ሰዓት ጀምሮ እስከ ሀዘኑ ፍፃሜ በባህሉ በተዋቀሩ ማህበራዊ ተቋሞች የሚከወኑ
ሥነርዓቶች አሉ። የእነዚህ በቅድመ ቀብር፣ በቀብርና ድህረቀብር የሚከወኑ ሥርዓቶችን የሚያሳዩ
መረጃዎች የተሰበሰቡት በቃለመጠይቅና በምልከታ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ሲሆኑ
መረጃዎቹ ከህይወት ዑደት የደረጃ ሽግግር አንፃር ተንትነዋል። በትንተናውም ሞተው በሚለዩና
ወደ “አያት ቅድመአያቶቻቸው በሚደመሩ” ወገኖች ሰበብ ህዝቡ ተሰባስቦ የሚከውናቸው
ድርጊቶች አብሮነቱን፣ መተጋገዙንና ፍቅሩን እንደሚያድስ ባህላዊ እሴቶቹን እንደሚጠብቅ
አጉልተው የሚያሳዩ መሆናቸውን መረዳት ተችሏል።
Downloads
Download data is not yet available.