“ቃላ” የሀላባ ሴቶች ባህላዊ ዘፈንና ማህበራዊ ፋይዳው
Abstract
የሀላባ ብሔረሰብ እንደሌሎቹ በኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔረሰቦች የባህል ባለጸጋ ሲሆን በስነቃል
ዘርፍ የሚመደቡ በርካታ የሚዜሙና የማይዜሙ ቃል ግጥሞች ያሉት ማህበረሰብ ነው። ከነዚህ
በቃል ግጥም ዘርፍ ከሚካተቱ የስነቃል ገጽታዎች መካከል የዚህ ጥናት ትኩረት የሆነው “ቃላ”
የሚባል በሴቶች ብቻ የሚከወን ባህላዊ ዘፈን ይገኛል። “ቃላ” በማህበረሰቡ ዘንድ ታዋቂ የሆኑ
ጀግኖች፣ ስመጥር ግለሰቦች እንዲሁም የእነዚህ ግለሰቦች ዘርና ጎሳ የሚሞገስበት፣ የሚወደስበትና
የሚደነቅበት የዘፈን ዓይነት ነው። “ቃላ” በሀላባ ብሔረሰብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅና በተወሰኑ
አጋጣሚዎች የሚዘፈን ነው።