Articles

የሃይማኖት መቻቻልን ማስተዋወቅ ለሰላማዊ አብሮነት በአርሲ ዞን ማሳያነት

Abstract

የጥናቱ ዋና አላማ፣ በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት መካከል በሰላማዊ አብሮነት ለመኖር
ያስቻሏቸው የመቻቻል መገለጫ ፎክሎሮችን ማስተዋወቅ ይሆናል። ኢትዮጵያ በብሔረሰቦቹዋ
ውስጥና መካከል በታሪክ የተገነባው የብዝኀ-ባህል የግንኙነት መስተጋብር ባሕርያት ምን
እንደሚመስሉ ተጠንተው አልተገለፁም፡፡ አይታወቁም፡፡ የዚህ ጥናት ዋና ትኩረት በሆነው
በአርሲ ዞን፣ በሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ውስጥ የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ
ማህበረሰቦች መካከል ባለው የመቻቻል እሴት ከፎክሎር አንፃር ማሳየት ነው። በክርስትና እና
በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል በሰላም ተከባብሮ ለመኖር ያስቻሏቸው የመቻቻል
ፎክሎር ምንድን ናቸው? በአርሲ ዞን በሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ለሰላማዊ አብሮነት
አስተዋጽዎ ያላቸው የመቻቻል ባህላዊ እሴቶች በተለይ እድር፣ ጡት መጣባትና ባህላዊ
እምነት ጥናቱ ያተኮረባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው። በማህበረሰቦች መካከል ያሉትን
የሃይማኖት ልዩነቶች በመቻቻል የሚመሩ፣ በባህል የተደነገጉና የተቁዋቁዋሙ ለዘላቂ ሰላም
መሠረትና ዋስትና ተግባራዊ ሕጎች ሆነው ይሠራሉ፡፡ ባህላዊ እሴቶቹ በተለይም በእስልምናና
በትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ‘መቻቻል’ የሚለውን ፅንሰ-ሀሳብ፣
መርህና ተግብራዊ ድርጊቶች ማለትም፡- አንዱ የሌላውን ኅልውና ተቀብሎ እውቅና መስጠትን፣
መከባባርን፣ መተሳሰብን፣ መረዳዳትን፣ መተባበርን፣ አብሮነትን፣ አንድነትንና ሰላምን፣ ወዘተ፣
የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡

Downloads

Download data is not yet available.

Related articles