Articles
የሰቆጣ ወረዳ አለባበስና አጊያጌጥ ለውጥና ቀጣይነት
- Journal ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
- Issue Vol 27 No 1 (2018): ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
- Published
- ISSN 2222-6028
Abstract
የዚሀ ጥናት አላማ በቁሳዊ ባህል ስር የሚጠቀሰውን የሰቆጣ ወረዳን አለባበስና አጊያጌጥ ለውጥና
ቀጣይነት መግለጽ ነው፡፡ ጥናቴን በሰቆጣ ወረዳ ላይ እንዳከናወን ያነሳሳኝ ምክንያትም
በወረዳው አለባበስና አጊያጌጥ ላይ የተጠና ጥናት ባለመኖሩና በሉላዊነትና ‹‹በዘመናዊነት››
ምክንያት ሀገረሰባዊ አለባበሱና አጊያጌጡ እየቀነሰና በሌሎች ዘመናዊ አልባሳትና አጊያጌጥ
እየተተካ በመሄዱ፣ የማህበረሰቡ መገለጫነት ሊጠፋ ስለሚችል እንዲሰነድ ለማድረግ ነው፡፡
የጥናቱ ዘዴ ዓይነታዊ ሲሆን በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያነት ያገለግሉትም ቃለ መጠይቅ፣
ምልከታ፣ ቡድን ተኮር ውይይትና ሰነድ ፍተሻ ናቸው፡፡ መረጃው የተሰበሰበው በመስክ ጉዞ ነው፡
፡ የጥናቱ ግኝት እንደሚያመለክተው ባህላዊ አለባበሱና አጊያጌጡ ባሁኑ ጊዜ ከሞላ ጎደል
የሚታየው በገጠር አካባቢ እንደሆነ ነው፤ ወደ ከተማ አካባቢ ግን ለውጡ ጎልቶ ይታያል፡፡
ስለሆነም ባህላዊ አለባበሱና አጊያጌጡ ገጽታውን ሳይለቅ እንዲቀጥል ማህበረሰቡና
የሚመለከታቸውው አካላት ለወጣቶች ማስተማርና ጠቀሜታውን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡
Downloads
Download data is not yet available.